Theater

Missing Attachment

ክረምትዎን በቴአትር ግሩም ትዝታ ያድርጉት! ለመሆኑ እቤትዎ አረፍ ያሉ የክረምት እንግዳዎን ቴአትር ጋብዘውታል? ከትምህርት አረፍ ያሉ እነዚህን ሎጋ፣ ለግላጋ ልጆችዎንስ ?ልጆችዎ ቴአትር አይተው አያውቁም እንዴ? ኧረ ይጋብዟቸው።ክረምቱን ከቤተሰብዎ ጋር ወደኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር!! ዛሬ ማክሰኞ ከምሽቱ 11: 30″ ሶስቱ አይጦች›› ቴአትር እርስዎን ይጠብቅዎታል። ግን “ሶስቱ አይጦች” ሲባል ምን ታይዎ ? መቁረጥ ፣መቀርጠጥ፣መቦጨቅ፣መበጣጠስ… አመላቸው የሆነ አይጦች? በፍጹም !ነገሩ ከዚህ ይለያል ፡፡ ምክንያቱም ኪነጥበብ ጉዳዩ ሰውና ህይወቱ ነዋ!‹‹የሰው ልጅን እንደ አይጥ? ቴአትር ጉድ አፈላ ?›› አይሉም፡፡ ይልቁንም ራስዎ የህን ማንነትዎን ማን እንደሠራልዎ ትኩር ብለው ያዩበታል እንጂ፡፡ የሰው ልጅን እንደ ፓቭሎቭ አይጥ በቤተ ሙከራ?! …. የሰው ልጅ ግን ተፈጥሮውን ነው ወይስ የጻፍንበትን? ይኼ ቴአትር አያመልጥዎ! ይገረሙበታል!ተዋንያኖቹስ ቢሆኑ አቦ ሲችሉበት! “ሶስቱ አይጦች”ዘወትር ማክሰኞ 11፡30 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር! ማክሰኞ ማለት ዛሬ ነው! ይታደሙ

Leave a Comment

Addis Events
addis events in addis ababa