
አንጋፋ የኪነ-ጥበብ ምሽት
ቀን ፡ ሰኔ 12/2016 ዓ.ም
ቦታ ፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል
ሰአት ፡ 11: 30
በታላቁ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል በየጊዜው የሚዘጋጀው የኪነ-ጥበብ መርሃ ግብር ሃያ ስምንተኛ ምሽቱን ከፍ ባለ ዝግጅት የፊታችን ረቡዕ ሰኔ 12/2016 ዓ.ም ያካሂዳል። በዕለቱም በተለያዩ የጥበብስራዎች የምናቃት ተወዳጇ አርቲስት መስከረም አበራ የአንድ ግጥም የአንድ ወግ የክብር እንግዳ ሆና በዝግጅቱ ላይ የምትገኝ ሲሆን የተለያዩ ግጥሞች ፣ ወግ ፣ ሙዚቃና ሞኖሎግ ለእናንተ ውድ ታዳሚዎች በባህል ማዕከል አዳራሽ ከቀኑ በ 11: 30 ጀምሮ ተሰናድተው ይጠብቃችኃል ።
ፕሮግራሙ ላይ ለመታደም የምትፈልጉ በአሁን ሰዓት የዩኒቨርስቲው ተማሪ ያልሆናችሁ የኪነ-ጥበብ አፍቃሪያን መግቢያው በ5ተኛ በር በኩል ነው ።
Share This Event


