
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ አውደርዕይ
ቀን ፡ ከሚያዝያ 7 – 13
ቦታ ፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢ
አስራ ስድስተኛው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ የመፅሐፍ አውደርዕይ እና ሽያጭ ከዛሬ ሰኞ ሚያዝያ 7 እስከ ፊታችን እሁድ ሚያዝያ 13 2016 ዓ.ም ለተከታታይ ሰባት ቀናት ስድስት ኪሎ በሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢ ውስጥ ይካሄዳል።
በዚህ የመፅሐፍ አውደርዕይ እና ሽያጭ ላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ ሰባት አዳዲስ መጻሕፍት ይዞ አውደርዕዩ ላይ ይገኛል።
የእነዚህ ሰባት አዳዲስ መጻሕፍት አዘጋጆችም ማክሰኞ ፣ ረቡዕና ሐሙስ ስለ መጻሕፍቶቻቸው ማብራሪያ የሚሰጡበት መርሐግብርም እንደተዘጋጀ አዲስ ኤቨንት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
በአውደርዕዩም በርካታ ከ30 በላይ አሳታሚዎችና አከፋፋዮች በቅርቡ የታተሙ፣ ከገበያ የጠፉ ፣ የህፃናት መጻሕፍት፣ የሐይማኖት መጻሕፍትን ይዘው ይገኛሉ ተብሏል።
Share This Event



