
አርቲስት ድርብወርቅ ሰይፉ የክብር እንግዳ የሆነችበት “መቅረዝ ሥነኪን” የኪነጥበብ ዝግጅት ሀሙስ ይካሄዳል አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎችን እያጣመር የዘለቀው መቅረዝ ሥነኪን ወርሀዊ የኪነጥበብ ዝግጅት ሀሙስ ሰኔ 6 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመጻሕፍትና ቤተመዛግብት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል። በዕለቱም እረኛዬን ጨምሮ በተለያዩ ፊልሞቿና ድራማዎቿ የምናውቃት አርቲስት ድርብወርቅ ሰይፉ የክብር እንግዳ ሆና የምትገኝ ሲሆን በተጨማሪም ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች የግጥም ፣የሙዚቃ እና የዳንስ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ። የዚህ ዝግጅት መግቢያ በነፃ ነው።
Share This Event



