የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን

             ኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን

        ቦታ ፡ ሻምፒየንስ አካዳሚ

        ቀን ፡ ሚያዚያ 5

 በሻምፒየንስ አካዳሚ የተዘጋጀው “የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን” ነገ ሚያዝያ 5 2016 ዓ.ም በአካዳሚው ቅጥር ግቢ ውስጥ ይካሄዳል ።
ይህ “ዓለምአቀፍ የኦቲዝም ቀን” ዛሬ ሚያዝያ 4 2016 ዓ.ም በአካዳሚው በሚገኙ ተማሪዎች እና መምህር ተከብሯል።
ሻምፒየንስ አካዳሚ ዓለም አቀፍ የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀንን አስመልክቶ፤ የተለያዩ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ከተጋባዥ እንግዶች፣ ከወላጆችና ተማሪዎች ጋር በመሆን ነገ ሚያዝያ 5 2016 ዓ.ም ይከበራል ተብሏል።
      ዛሬ በማዕከሉ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ወላጆች ልጆቻቸው ወደ ሻምፒየንስ አካዳሚ ከመግባታቸዉ በፊትና ከገቡ በኋላ ያላቸዉን ለዉጥ ያካፈሉ ሲሆን፤ በዚህም ልጆቻቸው ከመደበኛ ተማሪዎች ጋር  ተካተው መማራቸው በዕለት ተዕለት ተግባቦታቸው ላይ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣቱን ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።
እ.ኤ.አ. አፕሪል 02 የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን ሲሆን ሙሉ ወሩ ደግሞ የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር ነው።
በሀገራችን ስለ ኦቲዝም ያለው የማህበረሰባችን ግንዛቤ በጣም ደካማ እንደሆነ የተጠቆመ ሲሆን የዓለም ኦቲዝም ቀን ግንዛቤን ለማስጨበጥ የተዘጋጀ ቀን ነው።
ዓለም አቀፍ የኦቲዝም የግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን በየዓመቱ ከመጋቢት 24 ቀን እስከ ሚያዝያ 22 ድረስ በተለያዩ ክንውኖች ታስቦ እንደሚከበር ይታወቃል።
በሻምፒየንስ አካዳሚ ባለቤትና ስራ አስኪያጅ መዓዛ መንክር በኦቲዝም ላይ ትኩረት ያደረገ”ሁሉም በአንድ” የተሰኘ ተግባር ተኮር የህክምና መጽሐፍ ለአንባቢያን መድረሱ ይታወሳል።

 

advertise on addis events
Event Details
Photos
Event Details