“Bealu Germa” is to begin a short permanent run at the National Theatre

የ”በዓሉ ግርማ ቤርሙዳ” ተውኔት ለአጭር ጊዜ በቋሚነት በብሔራዊ ቴአትር መቅረብ ሊጀምር ነው

በውድነህ ክፍሌ ተደርሶ በተሻለ አሰፍ የተዘጋጀውና በቅርቡ በአንጋፋው የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ሲቀረብ የነበረው “በዓሉ ግርማ ቤርሙዳ” ተውኔት ከፊታችን ሐሙስ ግንቦት 29 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለአጭር ጊዜ በቋሚነት በአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ከምሽቱ 11:30 ጀምሮ መቅረብ እንደሚጀምር ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

በበዓሉ ግርማ የሕይወት ታሪክ ላይ ተመሥርቶ የተሠራው “ቤርሙዳ” ተውኔት የበዓሉ ግርማ ወዳጆች በተገኙበት ከወራት በፊት ጥቅምት 17 2016 ዓ.ም ነበረ በሀገር ፍቅር ቴአትር የተመረቀው።

ለወራትም በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ዘወትር እሁድ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በቋሚነት ለታዳሚያን ሲቀረብ ነበር።

በኮሪደር ልማቱ የተነሳም በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት የትርዒት አቅርቦት እንደተቋረጠ ይታወሳል።

advertise on addis events
Event Details
Event Details