
የነፍሰጡሮች የቁንጅና ውድድር!
ታዋቂ ኢቨንት አማካኝነት የተሰናዳው “ንግሥት” የተሰኘ መጠሪያ የተሰጠው በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሆነ የነፍሰጡሮች የቁንጅና ውድድር ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እና ከብሔራዊ የደምና ሕብረ ህዋስ ባንክ ጋር በመተባበር ማዘጋጀቱን አሳወቀ።
መርኃ ግብሩን ያሰናዳው ታዋቂ ኢቨንት እለት በትላንትናው እለት ጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ላይ እንደገለጸው
ለመውለድ የተዘጋጁ ነፍሰ ጡሮች ከሚያደርጉት የቁንጅና ውድድር ባሻገር የፋሽን ሾዎ ኘሮግራሞች በዲዛይነሮች በተዘጋጁ ቅንጡ አልባሳት በመጠቀም ይበልጥ በእርግዝና ወቅት አሳሳቢ በሆኑት የነፍሰጡር አልባሳት ተውበው የሚታዩበት ፣ ምቾትን ተጎናጽፈው እራሳቸውን የሚገልጹበት ፣ ለተለያዩ ስሜቶች ተጋላጭ የሆነውን ይህንን የእርግዝና ጊዜ በተዝናኖት የሚያሳልፉበት ፣ ብሎም ባለቤቶችቸዉ በሚጠየቁት የእርግዝና ነክ ጥያቄዎቸ አማካኝነት እየተዳኙ ተወዳድረው በርካታ አጓጊ ሽልማቶችን የሚያገኙበት መሆኑን አዘጋጆቹ ገልጸዋል።
“ንግሥት” የነፍሰጡሮች የፋሽን ሾዉ ውድድር ዋነኛ አላማው በሀገራችን በስፋት እየተስተዋለ ስለሚገኘው የእናቶች በእርግዝና እና በወሊድ ወቅት ህይወት ማለፍን አስመልክቶ ግንዛቤ መፍጠርን ተነሳሽነት በማድረግ የተዘጋጀ ፕርግራም መሆኑን በመግለጫው ተገልጿል።
የፊታችን መስከረም ወር በስካይ ላይት ሆቴል በሚደረገው
የነፍሰጡሮች የቁንጅና ውድድር ላይ ከእናቶችም ባሻገር አባቶችም የሚሳተፉ ሲሆን አዘጋጆቹ ሁሉም እናቶች ቆንጆዎች ናቸው ያሉ ሲሆን ነፍሰጡር እናቶች የሚወዳደሩት ባለቤቶቻቸው በሚመልሱት ጥያቄ ላይ የተመሠረተ ይሆናል።
በውድድሩ አንደኛ የምትወጣው እናት በቀጣይ አንድ አመት ታዋቂ ኢቨንት የንግስት አምባሳደር የምትሆን ሲሆን
ኘሮግራሙ ቀጣይነት እንዳለው አዘጋጆቹ ገልጸዋል።



