
“ለእርቃን ሩብ ጉዳይ” መጽሐፍ ምርቃት
የደራሲ ሕይወት እምሻው “ለእርቃን ሩብ ጉዳይ” የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ሐሙስ ሐምሌ 25 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት መደብር ውስጥ ይመረቃል።
ሐያ ስምንት ታሪኮችን የያዘው አዲሱ መጽሐፏ በ208 ገፆች ተቀንብቦ በ300 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ይቀርባል
ደራሲዋ ከዚህ ቀደም ባሪቾ ፣ ፍቅፍቂ ፣ ማታ ማታ የተሰኙ መጻሕፍትን ለንባብ አብቅታለች።
Share This Event


