ኮላዥ አዲስ መጽሐፍ

                        ኮላዥ አዲስ መጽሐፍ

ቀን ፡ ሚያዝያ 18 ቀን 2016ዓ.ም

ቦታ ፡ ግሩቭ ጋርደን

ሰአት ፡ 10:00 ሰዓት

መጽሐፉ የአጭር ልብ ወለድ ትረካዎች ስብስብ ሲሆን
በውስጡ የ የማኀበረሰባችን የዕለት ተዕለት ኑሮን ፣የህይወት ውጣ ውረዶችን ፤ ማኀበረሰባዊ ግንኙነትን ፍቅርን ፣ ወዳጅነትን ፣ ጉርብትናን እና ዝምድናን ፣ ፓለቲካዊ ትዝብት እና የመፍትሄ ጥቁምታን፣ ደራሲዋ በተያዩ የሀገራችን አካባቢዎች በሥራ ምከንያት በተንቀሳቀሰችበት ወቅት ያየችውን ያስተዋለችውን የሕይወት ሃቅን በጥበባዊ እይታ አገጣጥሞ ይዟል ።
ኮላዥ ከተለያዩ ምስሎች፣ ቅርፃች፣ ቁሶች እና ቀለማት የሚፈጠር በአንድ ገፅ ላይ የተቀናበረ የስዕል ጥበበ ነው።
የቃሉ መሰረት ፈረንሳይኛ ሲሆን ስርወ – ቃሉ ” ኮላ “፣ ማጣበቅ፣ መገጣጠም፣ መለጠፍ እንደማስት ነው።
ዘቢብ መልኬ ቀደም ሲል “ስብጥር” የተሰኘ የግጥሞች እና አጫጭር ልብወለዶች መድበል ያሳተመች ሲሆን “የፅጌ አበባ እና ሌሎች ተረቶች ” የሚል የልጆች መፅሀፍም አበርክታለች ።

 

advertise on addis events
Event Details
Photos
Event Details