የባህል ስፖርት ፌስቲቫል በአዲስ አበባ

                   የባህል ስፖርት ፌስቲቫል በአዲስ አበባ

  ቀን ፡ ከሚያዚያ 12 _20

ቦታ ፡ ኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ እና በጃን ሜዳ ስፖርት ትምህርት እና ስልጠና ማዕከል

21ኛው ኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶች ውድድር እና 17ኛው የባህል ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ከተማ ከሚያዚያ 12 ጀምሮ ይካሄዳል።
የኢፌድሪ ባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር እና የኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን በጥምረት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ 21ኛው የኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶች ውድድር እና 17ኛው የባህል ስፖርት ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስተናጋጅነት ከነገ ሚያዚያ 12 እስከ 20/2016ዓ.ም የባህል ስፖርቶች ልማት ለገፅታ ግንባታ በሚል መሪ ቃል ይካሄዳል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአስተናጋጅነት እድሉን በ2015 ዓ.ም ከተሰጠው ቀን ጀምሮ ከተማዋን በሚመጥን ፣ የሌሎች ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ተምሳሌት በሚሆን እና የባህል ስፖርታችንን በዓለም አቀፍ ደረጃ በምናስተውቅበት መንገድ ሰፊ ዝግጅት መደረጉን አቶ በላይ ደጀን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ተናግረዋል።
በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የተገኙት የኢፌድሪ ባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት ባህል ስፖርቶች የሃገራችንን ባህል፣ ወግ፣ ታሪክ እና እሴት ከማስተዋወቅ ባሻገር ለዘመናዊ ስፖርት መሰረት መሆናቸው ገልጸው የስፖርት ፖሊሲው ላይ በግልጽ የተቀመጠው መንግስት ባህላዊ ስፓርቶች የማጥናት ሕዝቡ እንዲጠቀምበት የማደረግ ተግባር አጠናክሮ እንደሚሰራ ገልጸዋል ፡፡

 

advertise on addis events
Event Details
  • Category
  • Address
    ኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ እና በጃን ሜዳ ስፖርት ትምህርት እና ስልጠና ማዕከል
Event Details
  • Category
  • Address
    ኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ እና በጃን ሜዳ ስፖርት ትምህርት እና ስልጠና ማዕከል