
“እሳት ወይ አበባ” ተውኔት ወደ መድረክ ሊመለስ ነው
በሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ግጥሞች ላይ የተመሰረተው “እሳት ወይ አበባ” ግጥማዊ ዳንስ ተውኔት በብሔራዊ ቴአትር ከሰኔ 14 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ መድረክ እንደሚመለስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።
“እሳት ወይ አበባ” የሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ግጥሞች ላይ መሰረት ያደረገ የግጥማዊ ዳንስ የሙከራ (Experimental) ቴአትር ነው።
ይህ ሙከራዊ ተውኔት ባሳለፍነው ጥቅምት 2 2016 ዓ.ም ነበር ዘወትር አርብ ሲቀረብበት ከነበረው የአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ የተሰናበትው።በምትኩም “የሁለት አሽከር ጌቶች” የተሰኘ ተውኔት ሲቀርብም ቆይቷል።
ኤቨንት አዲስ ድረገፅ እንዳረጋገጠው በሚቀጥለው ሳምንት ሰኔ 14 2016 ዓ.ም “እሳት ወይ አበባ ” ተውኔት ወደ መድረክ ተመልሶ በቋሚነት ዘወትር አርብ በ11:30 መቅረብ ይጀምራል ተብሏል።
ይህ ግጥማዊ ድራማ ከዚህ ቀደም በሀገር ፍቅር ቴአትር ትንሿ አዳራሽ ለታደሚያን ይቀርብ እንደነበር ይታወሳል።
Share This Event



