
የሠዓሊ ቤተል ጌቱ “ፍርሃት” የተሰኘ የሥነጥበብ አውደርዕይ ቅዳሜ መጋቢት 28 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በፖስት የሥዕል ማሳያ ውስጥ ለእይታ ይበቃል።
ሠዓሊዋም በማህበራዊ ትስስር ገጿ ” “ፍርሃት” ወይም “Fear” በሚል ርዕስ ረዥም ጊዜ ወስጄ ሳዘጋጃቸው የቆየኋቸው የሥዕል ሥራዎቼ በመጨረሻም መጋቢት 28፣ ቅዳሜ 8፡00 ሰዓት ላይ ቦሌ “Skylight” ሕንጻ ውስጥ በሚገኘው “Post – Gallery” ለዕይታ ይበቃሉ።
“ፍርሃት” ሰው በመኾን የምንጋራው ስሜት ነው። ይህ ውስብስብ ስሜት በሕይወታችን በተለያየ መንገድ ለሚከሰቱ ሁኔታዎች እንደ ሰው ልጅ የምንሰጠው ግብረ መልስ ወይም “response” ነው። በዋናነት ይህን ጥልቅና ዘወትር ዕንግዳ የኾነ ስሜት በካንቫሴ ላይ አንጸባርቂያለሁ። ከአክብሮት ጋር እንድትታደሙ እጋብዛለሁ” ብላለች።
Share This Event




