
ድምፅ ለሌላቸው ድምጽ እንሁናቸው ልዩ የእግር ጉዞ ተዘጋጀ
ቀን ፡ ሚያዚያ 6
ትኬት ፡ 400 ብር
ቦታ ፡ አኬዥያ ቪሌጅ
የትኩረት ለሴቶችና ለሕፃናት ማህበር”ድምፅ ለሌላቸዉ ደምፅ እንሁናቸው” በሚል መሪ ቃል ሚያዚያ 6 ቀን የእግር ጉዞ እንደሚያደርግ አስታወቀ።
ይህ የእግር ጉዞ በየአመቱ ልዩ ፍላጎት ያላቸዉን ህፃናት ለመደገፍ ግንዛቤ ለመፍጠር የአለምአቀፍ ኦቲዝም ቀን ለማሠብ አኬዥያ ቪሌጅ የእግር ጉዞ በሚል በየአመቱ በፈረንጆቹ April እንደሚካሄድ ተነግሯል፡፡
የፊታችን ሚያዝያ 6 ቀን 2016 ዓ.ም “ድምፅ ለሌላቸዉ ደምፅ እንሁናቸው” በሚል መሪ ቃል ባዘጋጀው የእግር ጉዞ መርሀ-ግብር ላይም ህብረተሰቡ እንዲሳተፍም ጥሪ አቅርቧል።
ማህበሩ ላለፉት 17 ዓመታት በአዲስ አበባና በክልል አካባቢዎች 17 ሺህ የሚደርሱ ወላጆቻቸዉን ላጡና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ሴቶች ድጋፍና ክትትል ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል።
በድርጅቱ ዉስጥ ተደራራቢ የጤና ችግር ያለባቸዉ 18 ሕፃናት የሚገኙ ሲኾን፣ ለነዚህ ሕፃናት የጤና ፣የምግብና የትምህርት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
ትኩረት ለሴቶችና ለሕናት ማህበር በኢትዮጵያ በአይነቱ ልዩ የኾነውን ተደራራቢ የሕፃናት የጤና ችግር ላለባቸውን የሚኾን 2932.86 ካሬ ላይ በተሰጠዉ ቦታ ላይ ማዕከል ገብቶ ያጠናቀቀ አጠናቋል። ተደራሽነቱንም በማስፋት G+9 ፎቅ ለመስራት እንዳቀደም አስታዉቋል።ማህበሩ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ወረዳ 13 ባስገነባው ማዕከልም ተደራራቢ የጤና ችግር ያለባቸዉ 260 ሕፃናትና ለ278 እናቶች በመደገፍ ላይ እንደሚገኙ ገልጿል።





