የጋዜጠኛ ሞሊቶ ኤልያስ አዲስ መፅሃፍ

                      የጋዜጠኛ ሞሊቶ ኤልያስ አዲስ መፅሃፍ

ቀን ፡ ሚያዚያ 18

ቦታ ፡ በወመዘክር አዳራሽ

ሰአት ፡ 10:00

የጋዜጠኛ ሞሊቶ ኤልያስ “ሉዱንዳ” የተሰኘ አዲስ የጠቅላላ እውቀት መጽሐፍ የፊታችን አርብ ለንባብ ይበቃል።
መጽሐፉ ጋዜጠኛ ሞሊቶ ኤልያስ ከደቡብ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት እስከ ፋና 98.1 በሰራባቸው ከ6 ለበለጡ ዓመታት ያዘጋጀው ለነበረው የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ መርሐግብር ይሰበስባቸው የነበሩ የጠቅላላ እውቀት መረጃዎችን በተደራጀ መልኩ በአንድ የያዘ ነው።
“ሉዱንዳ” መጽሐፍ በ17 ምዕራፎች ከ190 በላይ አስገራሚ መረጃዎች፣ አስደማሚ ክስተቶችንና ጠቃሚ መረጃዎችን ይዞ በ159 ገፅ በ300 ብር የጀርባ ዋጋ ለገበያ ይቀርባል።
በተለይ የንባብ ፍላጎት በተቀዛቀዘበትና ስለአንድ ነገር ለማወቅ ሰፋ ያለ ፅሁፍ አገላብጦ መረዳት የተራራ ያህል በከበደበት በዚህ ሰዓት፣ በርካታ የእውቀት ዘርፎችን የተመለከቱ መረጃዎችን በአንድ የያዘው ሉዱንዳ የመረጃ ብፌ ሆኖ ያገለግላል።
የመጽሐፉ ርዕስ ”ሉዱንዳ” የቃሉን ትርጓሜ የሀድይሳ ቃል ሆኖ የሁለት ቃላት ጥምር ነው።”ሉዱ” እና “ሁንዳ”ፍቺውም ጠቅላላ ዕውቀት የሚል አቻ ትርጉም ያለው ወይንም (ከሁሉም የተቀነጫጨበ ዕውቀት) እንደማለት ነው ።
“ሉዱንዳ” አርብ ሚያዚያ 18 በ10:00 በወ መዘክር አዳራሽ፣ አንጋፋና ወጣት ደራሲያን የመንግስት የስራ ሀላፊዎችና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል።
መፅሀፉ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በቅርቡ ሆሳዕና ከተማም ይመረቃል።

 

advertise on addis events
Event Details
Photos
Event Details