
ዓለም አቀፍ የወንዶች የሞዴሊንግ ውድድር በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ ሊካሄድ ነው፡፡
ቀን ፡ ሚያዚያ 12 2016
ቦታ ፡ ኖራ ሪዞርት
ስልክ ፡ +251933578367
የ – ONE AFRICA FASHION WEEK ዳይሬክተር የሆኑት ኢንተርናሽናል ሞዴል ሳዳም ቃሲም ” MAN OF THE GLOBE ETHIOPIA ውድድር በአፕሪል (April) 20/ 2024 በኖራ ሪዞርት ቢሾፍቱ-ኢትዮጰያ ይካሄዳል፡፡
MAN OF THE GLOBE INTERNATIONAL PAGEANT የሚባለው ካምፓኒ መቀመጫውን ኤዥያ ፍሊፔንስ ያደረገው በየዓመቱ ከተለያዩ አኅጉራት የወንድ ሞዴሎችን በማወዳደር አሸናፈውን በየዓመቱ እየመረጠ የሥራ እድልና የሞዴሊንግ ሥራን በዓለም አቀፍ እያስተዋወቀ የሚገኝ ካምፓኒ ነው::
ባለፈው ዓመት ማለትም በፈረንጆች ኖቨንበር 2023 ፍሊፒንስ ሃገር በተዘጋጀው ውድድር ኢትዮጵያን ወክሎ የተወዳደረው ኢንተርናሽናል ሞዴል ሳዳም ቃሲም ሃገሩን በመወከል በኢትዮጰያ ለመጀመርያ ጊዜ አሸናፊ ሆኖ የወርቅና የገንዘብ ሽልማት አግኝቶ መመለሱ ይታወቃል፡፡
ይህንን ውድድር በማሸነፍ ከ MAN OF THE GLOBE INTERNATIONAL PAGEANT ካምፓኒ ጋር የአንድ አመት የሥራ ውልና ለኢትዮጵያ ናሽናል ዳሬክተር ሆኖ እየሰራ ይገኛል፡፡
በዚህ ታላቅ መሠረት በቀጣዩ ዓመት፤ ማለትም በፈረንጆች ዲሴምበር 2024 ላይ በሚካሄደው MAN OF THE GLOBE INTERNATIONAL PAGEANT ላይ ኢትዮጰያን ወክሎ የሚወዳደር የወንድ ሞዴል ኢትዮጵያ ውስጥ በምናዘጋጀው ውድድር አሸናፊውን ኢትዮጵያን ወክሎ MAN OF THE GLOBE INTERNATIONAL PAGEANT በታይላንድ (ባንኮከ) ሃገር በሚዘጋጄው ውድደር ላይ የራሱን ስምና የሃገሩን ባህል፤ እሴትና ቱሪዝም እንድያስተዋውቅ ለማድርግ እየሰራን እንገኛለን፡፡
ይህንን ውድድር በኢትዮጰያ ለመጀመርያ ጊዜ እንድናዘጋጅ ምክንያት የሆነው ኢንተርናሽናል ሞዴል ሳዳም ቃሲም ኢትዮጵያ ሃገሩን ወከሎ MAN OF THE GLOBE INTERNATIONAL PAGEANT 2023 በማሸነፉ ምክንያት ነው::

ኢንተርናሽናል ሞዴል ሳዳም ቃሲም ካሁን በፊት በሞዴሊንግ ሥራ የተለያ ሥራዎችን ሲሰራ የነበረና አሁንም በመስራት ላይ የሚገኝ ሞዴል ነው፡፡ ለአብነትም ያህል ፋሽን ሾው፤ ኮሜርሻል ማስታወቂያ፤ የሙዚቃ ከሊፕ፤ የተለያዩ አጫጭር ፊልሞችና የራሱን ONE AFRICA FASHION WEEK የሚል ካምፓኒ አቋቁሞ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
ONE AFRICA FASHION WEEK በየአመቱ ከአዳዲስና ነባር ዲዛይነሮች ጋር በመሆን የተለያዩ የባህል አልባሳትን በዘመናዊ መልኩ ስርቶ ማህበርሰቡ ጋር ተወዳጅና ዘወትር እንዲለበስ ለማድረግ በየዓመቱ በፋሽን ሾው በማስተዋወቅ ላይ እንደነበር ይታወቃል፡፡
ዘንድሮም ለሦስተኛ ጊዜ MAN OF THE GLOBE ETHIOPIA ውድድር ጋር (በአንድ ቀን) ONE AFRICA FASHION WEEK ይካሄዳል፡፡
MAN OF THE GLOBE ETHIOPIA ውድድር እፕሪል (April) 20/ 2024 በኖራ ሪዞርት ቢሾፍቱ-ኢትዮጰያ ይካሄዳል፡፡
ONE AFRICA FASHION WEEK እና NORU MULTIMEDIA በአጋርነት ይህንን ኢቨንት እያዘጋጁ
ይገኛሉ፡፡
እዚህ ታሪካዊ ውድድር ላይ የተለያዩ የመንግስትና የግል ሚዲያዎች ፤ ሃገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ሞዴሎች የተለያዩ የአርት ባለሙያዎች፣ ባለ ሃብቶች፣ የመንግስት አካላትና ተጋባዥ እንግዶች ይገኙበታል፡፡
ኑ – አብረን እንሥራ” ሲሉ መግለጫ ሰጥተዋል።
Share This Event







