
“ባህላዊ ቅርስ አጠባበቅ ተግዳሮቶችና መፍትሔ ሀሳቦች” የተሰኘ ውይይት
ቀን ፡ ሚያዝያ 10
ሰአት ፡ ከቀኑ 10፡00
ቦታ ፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ እሸቱ ጮሌ መታሰቢያ አዳራሽ
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የፓናል ውይይት መድረክ
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በተለያዩ ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ርእሰ ጉዳዮች ላይ የኅብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግና ሳይንሳዊ አሠራሮችን ለማጎልበት ያለመ የወርሐዊ ገለፃና የፓናል ውይይት መድረኮችን ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡
አሁንም በኢትዮጵያ ከሚገኘው የአሜሪካን ኢምባሲ ከፐብሊክ ዲፕሎማሲ ክፍል ጋር በመተባበር ከሚያካሂዳቸው ተከታታይ መርሐግብሮች አንዱ የኾነውን የፓናል ውይይት “የባህላዊ ቅርሶች ጥበቃ ተግዳሮቶችና መፍትሔዎች” በተሰኘ ርእስ በዘርፉ ከፍተኛ ምሑራን አቅራቢነትና አወያይነት ያካሂዳል።
አቅራቢዎች፡-
ዶክተር ዮናስ በየነ
አወያይ፡-
ፕሮፌሰር ሽፈራው በቀለ
መርሐግብሩ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ እሸቱ ጮሌ መታሰቢያ አዳራሽ ሐሙስ ሚያዝያ 10 ሰዓት 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት እስከ 12፡00 ሰዓት ስለሚካሄድ በአካል ተገኝተው እንዲሳተፉ በአክብሮት ተጋብዘዋል።
Share This Event



