RAMADAN BAZAAR

ቢላሉል ሀበሺ የልማትና መረዳጃ እድር ከሀይፕሮፋይል ጋር በመተባበር ከየካቲት 22 እስከ መጋቢት 1 2016 የሚቆይ የረመዳን ባዛር አዘጋጅቷል።

በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማእከል በሚካሄደው በዚህ ታላቅ “ረመዳን ባዛር” ሁሉም እንዲሳተፍ ጥሪ የቀረበ ሲሆን የባዛሩ ገቢ በዋናነት ድርጅቱ እየሰራቸው ላሉ በርካታ የበጎ አድራጎት ስራዎች እንዲውል ታስቦ የተዘጋጀ ነው ተብሏል።

በፕሮግራሙ የመክፈቻ እና የመዝጊያ ዝግጅት ላይ በርካታ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በክብር እንግድነት እንደሚታደሙ እና የመግቢያ ዋጋም 100 ብር መሆኑ ተገልጿል።

advertise on addis events
Event Details
Photos
Event Details