የመጀመሪያው ዓመታዊ የዩኒቨርሲቲዎች የባሕል ማዕከላት ፌስቲቫል

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት የመጀመሪያው ዓመታዊ የዩኒቨርስቲዎች የባህል ማዕከላት ፌስቲቫል ዛሬ ጥር 27 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ቀናት እንደሚካሄድ ዩኒቨርስቲው አስታውቋል፡፡

“የፌስቲቫሉ ዋና ዓላማ በዩኒቨርስቲዎች መካከል  ትስስር መፈጠር” እንደሆነ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ባህል ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ እሸቱ ገልጽዋል፡፡

ይህ  ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆየው ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢ ውስጥ በሚገኘውና ለዚህ ዓላማ ታስቦ በተዘጋጀው የፋውንቴን መናፈሻው ፊትለፊት በልዩልዩ ዝግጅቶች እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

በዚህ ፌስቲቫል ላይ የጥናትና ምርምር ሲምፖዚየምና የኪነጥበብ ዝግጅቶች ይኖራሉ፡፡

በጥናትና ምርምር ሲምፖዚየም ላይ ለተከታታይ ሶስት ቀናት ስምንት ጥናታዊ ጹሑፎች በስምንት የዩኒቨርስቲው ፕሮፌሰሮች ይቀርባሉ፡፡

በኪነጥበብ ዝግጅቶች ደግሞ ከቀድሞ እስከ ዛሬ ያሉ ህብረ ዝማሬዎች፣ የዘመን ጨዋታዎች የግጥም መርሀግብር፣ ሰርከስ፣ የሙዚቃ ኮንሰርት(አብዲ ኪያር ፣ሃና ግርማ ፣ ጌታቸው ኃ/ማሪያም የተሳተፉበት)መርሃግብር ይካሄዳሉ፡፡

ከሲምፖዚየሙና ኪነጥበባዊ ዝግጅቱ በተጨማሪ ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የመጡ እንግዶች አዳዲስ የስነጥበብ ማዕከላት ጉብኝትም ተካቶውበታል፡፡

በፌስቲቫሉ ላይ የባህል ማዕከላት ያላቸው ዩኒቨርስቲዎች ጥሪ ተደርጎላቸዋል ተብሏል።

ከዚህም በኃላም ዩኒቨርስቲዎች በየተራ ኃላፊነት ወስደው የሚያዘጋጁት ዓመታዊ ክብረበዓል ሆኖም ይቀጥላልም ተብሏል።

ፌስቲቫሉን ዓለምአቀፍ የማድረግ እቅድ እንዳለም ተገልጿል።

 

 

 

 

 

advertise on addis events
Event Details
  • Start Date
    02/05/2024 5:00 am
  • End Date
    02/07/2024 12:00 am
  • Status
    Expired
  • Category
  • Address
    አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማእከል
Photos
Event Details
  • Start Date
    02/05/2024 5:00 am
  • End Date
    02/07/2024 12:00 am
  • Status
    Expired
  • Category
  • Address
    አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማእከል