
Water in ethiopia የሚል ርዕስ ያለው የስዕል ኤግዚቢሽን ለጎብኚዎች ክፍት ሆኗል
ሰባት ሰዓሊዎች ጥምር ስራዎቻቸውን እያቀረቡበት የሚገኘው ይሄው ኤግዚቢሽን እስከ የካቲት 1 ቀን 2016 ዓ/ም በገብረክርስቶስ ደስታ አርት ሙዚየም ክፍት ሆኖ ይቆያል
የኤግዚቢሽኑ አዘጋጅ ጎተ ኢንስቲትዩት ሲሆን ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡትም አቤኔዘር ተፈራ ፣ አሸናፊ መስቲካ ፣ በዕምነት ፍቃዱ ፣ ካርሎስ ኤርቶላ ፣ ዳዊት ተሾመ ፣ መቅደስ አባቡ እና ሚኪያስ አለማየሁ ናቸው።
ኤግዚቢሽኑ ለጥበብ አፍቃሪዎች በሙሉ ክፍት እንደሆነም ከአዘጋጆቹ ሰምተናል
መግቢያውም ነጻ ነው ተብሏል
Share This Event



